ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 14:23-29 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. “የጃርት መኖሪያ፣ረግረጋማ ቦታ አደርጋታለሁ፤በጥፋትም መጥረጊያ እጠርጋታለሁ”ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

24. የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ምሎአል፤“እንደ ዐቀድሁት በርግጥ ይከናወናል፤እንደ አሰብሁትም ይሆናል።

25. አሦርን በምድሬ ላይ አደቃለሁ፤በተራራዬም ላይ እረግጠዋለሁ፤ቀንበሩ ከሕዝቤ ላይ ይነሣል፤ሸክሙም ከትከሻቸው ላይ ይወርዳል።”

26. ለምድር ሁሉ የታሰበው ዕቅድ ይህ ነው፤በአሕዛብም ሁሉ ላይ የተዘረጋው እጅ ይኸው ነው።

27. የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አስቦአል፤ማንስ ያግደዋል?እጁም ተዘርግቶአል?ማንስ ይመልሰዋል?

28. ንጉሡ አካዝ በሞተበት ዓመት እንዲህ የሚል ንግር መጣ፤

29. “እናንት ፍልስጥኤማውያን ሆይ፤የመታችሁ በትር ስለ ተሰበረ ሁላችሁ ደስ አይበላችሁ፤ከእባቡ ሥር እፉኝት ይወጣልና፤ፍሬውም ተወርዋሪ መርዘኛ እባብ ይሆናል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 14