ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 14:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ለያዕቆብ ይራራለታል፤እስራኤልን እንደ ገና ይመርጠዋል፤በራሳቸውም አገር ያኖራቸዋል።መጻተኞች አብረዋቸው ይኖራሉ፤ከያዕቆብም ቤት ጋር ይተባበራሉ።

2. አሕዛብም ይወስዷቸዋል፤ወደ ገዛ ስፍራቸውም ይመልሷቸዋል።የእስራኤል ቤት አሕዛብን ርስት ያደርጓቸዋል፤ በእግዚአብሔርም ምድር ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎች አድርገው ይገዟቸዋል፤የማረኳቸውን ይማርኳቸዋል፤የጨቈኗቸውንም ይገዟቸዋል።

3. እግዚአብሔር ከሥቃይህ፣ ከመከራህና ከጽኑ ባርነትህ ባሳረፈህ ቀን፣

4. በባቢሎን ንጉሥ ላይ ትሣለቃለህ፤ እንዲህም ትላለህ፤ጨቋኙ እንዴት አበቃለት!አስገባሪነቱስ እንዴት አከተመ!

5. እግዚአብሔር የክፉዎችን ዘንግ፣የገዦችንም በትረ መንግሥት ሰብሮአል፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 14