ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 10:27-34 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

27. በዚያን ቀን ሸክማቸው ከትከሻህ፣ቀንበራቸውም ከዐንገትህ ላይ ይነሣል፤ከውፍረትህም የተነሣቀንበሩ ይሰበራል።

28. ወደ ዐያት ይገባሉ፣በሚግሮን ያልፋሉ፤ጓዛቸውንም በማክማስ ያከማቻሉ።

29. መተላለፊያውን ዐልፈው እንዲህ ይላሉ፤“በጌባዕ ሰፍረን እናድራለን።”ራማ ደነገጠች፤የሳኦል ከተማ ጊብዓ ሸሸች።

30. የጋሊም ሴት ልጅ ሆይ፤ ጩኺላይሻ ሆይ፤ አድምምስኪን ዓናቶት ሆይ፤ መልሺላ

31. ማድሜናህ በሽሽት ላይ ነች፤የጌቢም ሕዝብ ሊደበቅ ይሮጣል።

32. በዚህ ቀን ኖብ ይደርሳሉ፤እጃቸውን በኢየሩሳሌም ኰረብታ፣በጽዮን ሴት ልጅ ተራራ ላይ በዛቻነቀነቁ።

33. እነሆ፤ ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣በታላቅ ኀይል ቅርንጫፎችን ይቈራርጣል፤ረጃጅም ዛፎች ይገነደሳሉ፤ከፍ ከፍ ያሉትም ይወድቃሉ።

34. ጥቅጥቅ ያለውን ደን በመጥረቢያ ይቈራርጣል፤ሊባኖስም በኀያሉ ፊት ይወድቃል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 10