ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 1:20-28 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. እምቢ ብላችሁ ብታምፁ ግንሰይፍ ይበላችኋል።” የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና።

21. ታማኝ የነበረችው ከተማእንዴት አመንዝራ እንደሆነች ተመልከቱቀድሞ ፍትሕ የሞላባት፣ጽድቅ የሰፈነባት ነበረች፤አሁን ግን የነፍሰ ገዳዮች ማደሪያ ሆነ

22. ብርሽ ዝጎአል፣ምርጥ የወይን ጠጅሽ ውሃ ገባው፤

23. ገዥዎችሽ ዐመፀኞችናየሌባ ግብረ ዐበሮች ናቸው፤ሁሉም ጒቦን ይወዳሉ፤እጅ መንሻንም በብርቱ ይፈልጋሉ፤አባት ለሌላቸው አይቆሙም፤የመበለቶችንም አቤቱታ አይሰሙም።

24. ስለዚህ ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣የእስራኤል ኀያል እንዲህ ይላል፤“በባላንጣዎቼ ላይ ቍጣዬን እገልጣለሁ፤ጠላቶቼንም እበቀላለሁ።

25. እጄን በአንቺ ላይ አነሣለሁ፣ዝገትሽን ፈጽሜ አጠራለሁ፤ጒድፍሽንም ሁሉ አስወግዳለሁ።

26. ፈራጆችሽን እንደ ጥንቱ፣አማካሪዎችሽንም እንደ ቀድሞው እመልሳለሁ፤ከዚያም የጽድቅ መዲና፣የታመነች ከተማተብለሽ ትጠሪያለሽ።

27. ጽዮን በፍትሕ፣በንስሓ የሚመለሱ ነዋሪዎቿም በጽድቅ ይዋጃሉ።

28. ዐመፀኞችና ኀጢአታኞች ግን በአንድነት ይደቃሉ፤ እግዚአብሔርንም የሚተዉ ይጠፋሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 1