ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 1:13-26 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. ከንቱውን መባ አታቅርቡ፤ዕጣናችሁን እጸየፋለሁ፤የወር መባቻ በዓላችሁን፣ሰንበቶቻችሁን፣ ጉባኤያችሁንናበክፋት የተሞላውን ስብሰባችሁን መታገሥአልቻልሁም።

14. የወር መባቻችሁንና የተደነገጉ በዓሎቻችሁንነፍሴ ጠልታለች፤ሸክም ሆነውብኛል፤መታገሥም አልቻልሁም።

15. እጆቻቸሁን ለጸሎት ወደ እኔ ስትዘረጉ፣ዐይኖቼን ከእናንተ እሰውራለሁ፤አብዝታችሁ ብትጸልዩም እንኳ አልሰማችሁም፤እጆቻችሁ በደም ተበክለዋል፤

16. ታጠቡ፤ ራሳችሁንም አንጹ፤ክፉ ሥራችሁን ከፊቴ አርቁ፤ክፉ ማድረጋችሁን ተዉ፤

17. መልካም ማድረግን ተማሩ፤ፍትሕን እሹ፣የተገፉትን አጽናኑ፤አባት ለሌላቸው ቁሙላቸው፤ለመበለቶችም ተሟገቱ።

18. “ኑና እንዋቀስ”ይላል እግዚአብሔር፤“ኀጢአታችሁ እንደ ዐለላ ቢቀላእንደ በረዶ ይነጣል፤እንደ ደም ቢቀላምእንደ ባዘቶ ነጭ ይሆናል።

19. እሺ ብትሉ፣ ብትታዘዙምየምድርን በረከት ትበላላችሁ፤

20. እምቢ ብላችሁ ብታምፁ ግንሰይፍ ይበላችኋል።” የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና።

21. ታማኝ የነበረችው ከተማእንዴት አመንዝራ እንደሆነች ተመልከቱቀድሞ ፍትሕ የሞላባት፣ጽድቅ የሰፈነባት ነበረች፤አሁን ግን የነፍሰ ገዳዮች ማደሪያ ሆነ

22. ብርሽ ዝጎአል፣ምርጥ የወይን ጠጅሽ ውሃ ገባው፤

23. ገዥዎችሽ ዐመፀኞችናየሌባ ግብረ ዐበሮች ናቸው፤ሁሉም ጒቦን ይወዳሉ፤እጅ መንሻንም በብርቱ ይፈልጋሉ፤አባት ለሌላቸው አይቆሙም፤የመበለቶችንም አቤቱታ አይሰሙም።

24. ስለዚህ ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣የእስራኤል ኀያል እንዲህ ይላል፤“በባላንጣዎቼ ላይ ቍጣዬን እገልጣለሁ፤ጠላቶቼንም እበቀላለሁ።

25. እጄን በአንቺ ላይ አነሣለሁ፣ዝገትሽን ፈጽሜ አጠራለሁ፤ጒድፍሽንም ሁሉ አስወግዳለሁ።

26. ፈራጆችሽን እንደ ጥንቱ፣አማካሪዎችሽንም እንደ ቀድሞው እመልሳለሁ፤ከዚያም የጽድቅ መዲና፣የታመነች ከተማተብለሽ ትጠሪያለሽ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 1