ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 1:10-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. እናንተ የሰዶም ገዦች፤የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤እናንተ የገሞራ ሰዎች፤ የእግዚአብሔርን ሕግ አድምጡ።

11. “የመሥዋዕታችሁ ብዛትለእኔ ምኔ ነው?” ይላል እግዚአብሔር።“የሚቃጠለውን የአውራ በግናየሰቡ እንስሳትን ስብ ጠግቤአለሁ፤በበሬ፣ በበግ ጠቦትና በፍየል ደም ደስአልሰኝም።

12. በፊቴ ለመቅረብ ስትመጡ፣ይህን ሁሉ እንድታመጡ፣የመቅደሴን ደጅ እንድትረግጡ ማን ጠየቃችሁ?

13. ከንቱውን መባ አታቅርቡ፤ዕጣናችሁን እጸየፋለሁ፤የወር መባቻ በዓላችሁን፣ሰንበቶቻችሁን፣ ጉባኤያችሁንናበክፋት የተሞላውን ስብሰባችሁን መታገሥአልቻልሁም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 1