ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

አብድዩ 1:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ጌታ እግዚአብሔር ስለ ኤዶም እንዲህ ይላል፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ መልእክት ሰምተናል፤መልእክተኛውም ወደ አሕዛብ ተልኮ እንዲህብሎአል፤“ተነሡ፤ እርሷን ለመውጋት እንውጣ።”

2. “እነሆ፤ በአሕዛብ መካከል ታናሽ አደርግሃለሁ፤እጅግ የተናቅህ ትሆናለህ።

3. አንተ በሰንጣቃ ዐለት ውስጥየምትኖር፣መኖሪያህንም በከፍታ ስፍራ ያደረግህ፣ለራስህም፣“ማን ወደ ምድር ሊያወርደኝ ይችላል?” የምትል፣የልብህ ትዕቢት አታልሎሃል።

4. እንደ ንስር መጥቀህ ወደ ላይ ብትወጣ፣ጐጆህንም በከዋክብት መካከል ብታደርግ፣ከዚያ አወርድሃለሁ”ይላል እግዚአብሔር።

5. “ሌቦች ወደ አንተ ቢመጡ፣ዘራፊዎችም በሌሊት ቢገቡ፣የሚሰርቁት የሚፈልጉትን ያህል ብቻ አይደለምን?ወይን ለቃሚዎች ወደ አንተ ቢመጡ፣ጥቂት ቃርሚያ አይተዉምን?አንተ ግን ምንኛ ጥፋት ይጠብቅሃል!

6. ዔሳው ግን እንዴት ተዘረፈ?የሸሸገውስ ሀብት ምንኛ ተመዘበረ!

7. ወዳጆችህ ሁሉ ወደ ድንበር ይገፉሃል፤ጓደኞችህ ያታልሉሃል፤ ያሸንፉህማል፤እንጀራህን የበሉ ወጥመድ ይዘረጉብሃል፤አንተ ግን አታውቀውም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ አብድዩ 1