ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

አስቴር 8:12-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. አይሁድ በመላው የንጉሥ ጠረክሲስ አውራጃ ሁሉ ይህን እንዲፈጽሙ የተወሰነው አዳር በተባለው በዐሥራ ሁለተኛው ወር ዐሥራ ሦስተኛ ቀን ነበር።

13. አይሁድ በዚያን ቀን ጠላቶቻቸውን ለመበቀል ዝግጁ እንዲሆኑ፣ የዋናው ዐዋጅ ቅጅ ሕግ ወደየአውራጃው እንዲላክና የየአገሩም ሕዝብ እንዲያውቀው ተደረገ።

14. በቤተ መንግሥቱ ፈረሶች የተቀመጡ መልእክተኞችም፣ በንጉሡ አስቸኳይ ትእዛዝ ጋልበው ወጡ፤ ዐዋጁም በሱሳ ግንብ ተነገረ።

15. መርዶክዮስ ሰማያዊና ነጭ የቤተ መንግሥት ልብስ ለብሶ፣ ትልቅ የወርቅ አክሊል ደፍቶ፣ ከቀጭን በፍታና ከሐምራዊ ግምጃ የተሠራ መጐናጸፊያ ተጐናጽፎ ከንጉሡ ፊት ወጣ፤ የሱሳ ከተማም ደስታ የተሞላበት በዓል አከበረች።

16. ጊዜውም ለአይሁድ የደስታና የፈንጠዝያ፣ የተድላና የክብር ወቅት ሆነላቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ አስቴር 8