ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

አሞጽ 7:15-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. እግዚአብሔር ግን የበግ መንጋ ከምጠብቅበት ቦታ ወስዶ፣ ‘ሂድና ለሕዝቤ ለእስራኤል ትንቢት ተናገር’ አለኝ፤

16. እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ።አንተ፣ “ ‘በእስራኤል ላይ ትንቢት አትናገር፤በይስሐቅም ቤት ላይ አትስበክ’ ትላለህ።

17. “ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤”‘ሚስትህ በከተማዪቱ ውስጥ ጋለሞታ ትሆናለች፤ወንዶችና ሴቶች ልጆችህም በሰይፍ ይወድቃሉ፤ምድርህም እየተለካ ይከፋፈላል፤አንተ ራስህ በረከሰ ምድር ትሞታለህ፤እስራኤልም ከትውልድ አገሩ፣ተማርኮ ይሄዳል።’ ”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ አሞጽ 7