ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

አሞጽ 4:4-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. “ወደ ቤቴል ሂዱና ኀጢአትን ሥሩ፤ወደ ጌልገላም ሂዱና ኀጢአትን አብዙ፤በየማለዳው መሥዋዕቶቻችሁን፣በየሦስቱ ዓመት ዐሥራታችሁን አቅርቡ።

5. እርሾ ያለበትን እንጀራ የምሥጋናመሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ፤በፈቃዳችሁም በምታቀርቡት ቊርባን ተመኩ፤እናንት እስራኤላውያን በእነርሱም ተኵራሩ፤ ማድረግ የምትወዱት ይህን ነውና፤”ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

6. በየከተማው ሆዳችሁን ባዶ አደረግሁት፤በየመንደሩም የምትበሉትንአሳጣኋችሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም”ይላል እግዚአብሔር።

7. “መከር ሊደርስ ሦስት ወር ሲቀረውም፣ዝናብ ከለከልኋችሁ፤በአንዱ ከተማ ላይ አዘነብሁ፤በሌላው ላይ ግን እንዳይዘንብአደረግሁ፤ አንዱ ዕርሻ ሲዘንብለት፣ሌላው ዝናብ አጥቶ ደረቀ።

8. ሰዎች ውሃ ፍለጋ ከከተማ ወደ ከተማ ባዘኑ፣ይሁን እንጂ ጠጥተው አልረኩም፤እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፤”ይላል እግዚአብሔር።

9. “የአትክልትና የወይን ቦታዎቻችሁን ብዙ ጊዜ መታሁ፤በዋግና በአረማሞም አጠፋኋቸው፤አንበጦችም የበለስና የወይራ ዛፎቻችሁን በሉ፤እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፤”ይላል እግዚአብሔር።

10. “በግብፅ ላይ እንዳደረግሁት፣መቅሠፍትን ላክሁባችሁ፤ከተማረኩት ፈረሶቻችሁ ጋር፣ጐልማሶቻችሁን በሰይፍ ገደልሁ፤የሰፈራችሁ ግማት አፍንጫችሁ እንዲገባ አደረግሁ፤እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም”ይላል እግዚአብሔር።

11. “ሰዶምንና ገሞራን እንደ ገለበጥኋቸው፣አንዳንዶቻችሁን ገለበጥሁ፤ከእሳት እንደ ተነጠቀ ትንታግ ሆናችሁ፤እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፤”ይላል እግዚአብሔር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ አሞጽ 4