ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

አሞጽ 2:10-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. “የአሞራውያንን ምድር ልሰጣችሁ፣ከግብፅ አወጣኋችሁ፤አርባ ዓመትም በምድረ በዳ መራኋችሁ።

11. ደግሞም ነቢያትን ከወንዶች ልጆቻችሁ መካከል፣ናዝራውያንንም ከጐልማሶቻችሁ መካከል አስነሣሁ፤የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፤ ይህ እውነት አይደለምን?”ይላል እግዚአብሔር።

12. “እናንተ ግን ናዝራውያኑን የወይን ጠጅ አጠጣችኋቸው፤ነቢያቱንም ትንቢት እንዳይናገሩ አዘዛችኋቸው።

13. “እነሆ፤ በእህል የተሞላ ጋሪ እንደሚያደቅ፣እኔም አደቃችኋለሁ።

14. ፈጣኑ አያመልጥም፤ብርቱውንም ብርታቱ አይረዳውም፤ኀያሉም ነፍሱን አያድንም።

15. ቀስተኛው በቦታው ጸንቶ አይቆምም፤ፈጣኑም ተዋጊ ሮጦ አያመልጥም፤ፈረሰኛውም ነፍሱን አያድንም።

16. ጐበዞቹ ተዋጊዎች እንኳ፣በዚያ ቀን ዕራቁታቸውን ይሸሻሉ፤”ይላል እግዚአብሔር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ አሞጽ 2