ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

አሞጽ 1:10-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. ምሽጎችዋን እንዲበላ፣በጢሮስ ቅጥሮች ላይ እሳት እሰዳለሁ።”

11. እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ስለ ሦስቱ የኤዶም ኀጢአት፣ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቊጣዬን አልመልስም፤ርኅራኄን በመንፈግ፣ወንድሙን በሰይፍ አሳዶታልና፤የቊጣውንም ነበልባል ሳይገድብ፣መዓቱን ሳያቋርጥ አውርዶበታልና፤

12. የባሶራን ምሽጎች እንዲበላ፣በቴማን ቅጥሮች ላይ እሳት እሰዳለሁ።”

13. እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ስለ ሦስቱ የአሞን ኀጢአት፣ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቊጣዬን አልመልስም፤ድንበሩን ለማስፋት፣የገለዓድን ነፍሰ ጡር ሴቶች ሆድ ቀዶአልና።

14. በጦርነት ቀን በጩኸት ውስጥ፣በማዕበል ቀን በዐውሎ ነፋስ ውስጥ፣ምሽጎቿን እንዲበላ፣በረባት ቅጥሮች ላይ እሳት እሰዳለሁ።

15. ንጉሥዋ ከሹማምንቱ ጋር፣በአንድነት ተማርኮ ይሄዳል፣”ይላል እግዚአብሔር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ አሞጽ 1