ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ናሆም 3:10-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. ይሁን እንጂ በምርኮ ተወሰደች፤ተሰዳም ሄደች።በየመንገዱ ማእዘን ላይ፣ሕፃናቷ ተፈጠፈጡ፤በመሳፍንቷ ላይ ዕጣ ተጣለ፤ታላላቅ ሰዎቿ ሁሉ በሰንሰለት ታሰሩ።

11. አንቺ ደግሞ ትሰክሪያለሽ፤ትደበቂያለሽ፣ከጠላትም መሸሸጊያ ትፈልጊያለሽ።

12. ምሽጎችሽ ሁሉ ሊበሉ እንደ ደረሱየመጀመሪያ በለስ ፍሬ ናቸው፤በሚወዛወዙበት ጊዜ፣ፍሬዎቹ በበላተኛው አፍ ውስጥ ይወድቃሉ።

13. እነሆ፤ ጭፍሮችሽ፣ሁሉም ሴቶች ናቸው!የምድርሽ በሮች፣ለጠላቶችሽ ወለል ብለው ተከፍተዋል፤መዝጊያዎቻቸውንም እሳት በልቶአቸዋል።

14. ለከበባው ውሃ ቅጂ፤መከላከያሽን አጠናክሪ፤የሸክላውን ዐፈር ፈልጊ፤ጭቃውን ርገጪ፤ጡቡንም ሥሪ።

15. በዚያ እሳት ይበላሻል፤ሰይፍ ይቈርጥሻል፤እንደ ኵብኵባም ይግጥሻል።እንደ ኵብኵባ እርቢ፤እንደ አንበጣም ተባዢ።

16. ከሰማይ ከዋክብት እስኪበልጡ ድረስ፣የነጋዴዎችሽን ቊጥር አበዛሽ፤ምድሪቱን ግን እንደ አንበጣ ግጠው አሟጠጡ፤ከዚያም በረው ሄዱ።

17. ጠባቂዎችሽ እንደ አንበጣ፣መኳንንቶችሽም በብርድ ቀንበቅጥር ሥር እንደሚቀመጥ ኵብኵባ ናቸው፤ፀሓይ ሲወጣ ግን ይበራሉ፤የት እንደሚበሩም አይታወቅም።

18. የአሦር ንጉሥ ሆይ፤ እረኞችህ አንቀላፉ፤መኳንንትህ ዐርፈው ተኙ፤ሕዝብህ ሰብሳቢ አጥተው፣በተራራ ላይ ተበትነዋል።

19. ቊስልህን ሊፈውስ የሚችል የለም፤ስብራትህም ለሞት የሚያደርስ ነው፤ስለ አንተ የሰማ ሁሉ፣በውድቀትህ ደስ ብሎት ያጨበጭባል፤ወሰን የሌለው ጭካኔህ፣ያልነካው ማን አለና?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ናሆም 3