ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ናሆም 1:11-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ነነዌ ሆይ፤ በእግዚአብሔር ላይ የሚያሤር፣ክፋትንም የሚመክር፣ከአንቺ ዘንድ ወጥቶአል።

12. እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ምንም ኀይለኞችና ብዙዎች ቢሆኑም፣ይቈረጣሉ፤ ይጠፋሉም።ይሁዳ ሆይ፤ ከዚህ በፊት ባስጨንቅህም፣ከእንግዲህ አላስጨንቅህም።

13. አሁንም ቀንበራቸውን ከዐንገትህ ላይ አንሥቼ እሰብራለሁ፤የታሰርህበትንም ሰንሰለት በጥሼ እጥላለሁ።”

14. አንቺ ነነዌ፤ እግዚአብሔር ስለ አንቺ እንዲህ ብሎ አዞአል፤“ስም የሚያስጠራ ትውልድ አይኖራችሁም፤በአማልክቶቻችሁ ቤት ያሉትን፣የተቀረጹትን ምስሎችና ቀልጠው የተሠሩትን ጣዖታት እደመስሳለሁ፤መቀበሪያህን እምስልሃለሁ፤አንተ ክፉ ነህና።

15. እነሆ፤ የምሥራች የሚያመጣው፣ሰላምን የሚያውጀው ሰው እግር፣በተራሮች ላይ ነው፤ይሁዳ ሆይ፤ በዓላትህን አክብር፤ስእለትህንም ፈጽም፤ከእንግዲህ ክፉዎች አይወሩህም፤እነርሱም ፈጽመው ይጠፋሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ናሆም 1