ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ነህምያ 12:10-25 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. ኢያሱ ዮአቂምን ወለደ፤ ዮአቂም ኤልያሴብን ወለደ፤ ኤልያሴብ ዮአዳን ወለደ፤

11. ዮአዳ ዮናታንን ወለደ፤ ዮናታንም ያዱአን ወለደ።

12. በዮአቂም ዘመን የካህናቱ ቤተ ሰብ አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ከሠራያ ቤተ ሰብ፣ ምራያ፤ከኤርምያስ፣ ሐናንያ፤

13. ከዕዝራ፣ ሜሱላም፤ከአማርያ፣ ይሆሐናን፤

14. ከሙሊኪ፣ ዮናታን፤ከሰብንያ፣ ዮሴፍ፤

15. ከካሪም፣ ዓድና፤ከመራዮት፣ ሔልቃይ፤

16. ከአዶ፣ ዘካርያስ፤ከጌንቶን፣ ሜሱላም፤

17. ከአብያ፣ ዝክሪ፤ከሚያሚንና ከሞዓድያ፣ ፈልጣይ፤

18. ከቢልጋ፣ ሳሙስ፤ከሸማያ፣ ዮናታን፤

19. ከዮያሪብ፣ መትናይ፤ከዮዳኤ፣ ኦዚ፤

20. ከሳላይ፣ ቃላይ፤ከዓሞቅ፣ ዔቤር፤

21. ከኬልቅያስ፣ ሐሸብያ፤ከዮዳኤ፣ ናትናኤል።

22. በኤሊያሴብ፣ በዮአዳ፣ በዮሐናንና በያዱአ ዘመን የሌዋውያኑ ቤተ ሰብ አለቆችና ካህናቱ፣ በፋርሳዊው በዳርዮስ ዘመነ መንግሥት ተመዝግበው ነበር።

23. ከሌዋውያን ዘሮች መካከል እስከ ኤሊያሴብ ልጅ እስከ ዮሐናን ድረስ ያሉት የየቤተ ሰቡ ኀላፊዎች በታሪክ መጽሐፍ ተመዝግበው ነበር።

24. የሌዋውያኑ መሪዎች ሐሸብያ፣ ሰራብያ፣ የቀድምኤል ልጅ ኢያሱ ነበሩ፤ እነርሱም ከወንድሞቻቸው ፊት ለፊት ሆነው የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት በሰጠው መመሪያ መሠረት እየተቀባበሉ ውዳሴና ምስጋና ያቀርቡ ነበር።

25. በቅጥሩ በሮች አጠገብ ያሉትን ዕቃ ቤቶች የሚጠብቁት ዘቦች ደግሞ መታንያ፣ በቅቡቅያ፣ አብድዩ፣ ሜሱላም፣ ጤልሞንና ዓቁብ ነበሩ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ነህምያ 12