ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሶፎንያስ 3:4-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ነቢያቷ ትዕቢተኞች፣አታላዮችም ናቸው፤ካህናቷ መቅደሱን ያረክሳሉ፣በሕግም ላይ ያምፃሉ።

5. በእርሷ ውስጥ ያለው እግዚአብሔር ጻድቅ ነው፤ፈጽሞ አይሳሳትም፤በየማለዳው ቅን ፍርድ ይሰጣል፤በየቀኑም አይደክምም፤ዐመፀኞች ግን ዕፍረት አያውቁም።

6. “ሕዝቦችን አጥፍቻለሁ፤ምሽጋቸው ተደምስሶአል፤ማንም እንዳያልፍባቸው፣መንገዳቸውን ባድማ አደረግሁ፤ከተሞቻቸው ተደምስሰዋል፤አንድም ሰው የለም፤ ነዋሪም ከቶ አይገኝባቸውም።

7. እኔም ከተማዪቱን፣‘በእርግጥ ትፈሪኛለሽ፤ዕርምትም ትቀበያለሽ’ አልኋት፤ስለዚህ መኖሪያዋ አይጠፋም፤ቅጣቴም ሁሉ በእርሷ ላይ አይደርስም።እነርሱ ግን በሚያደርጉት ሁሉ፣ክፋትንም በመፈጸም እየተጉ ሄዱ።

8. እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ስለዚህ እስከምፈርድበት ቀን ድረስጠብቁኝ፤አሕዛብን ላከማች፣መንግሥታትን ልሰበስብ፣መዓቴንና ጽኑ ቊጣዬን፣በላያቸው ላፈስ ወስኛለሁ፤በቅናቴ ቍጣ እሳት፣መላዋ ምድር ትቃጠላለችና።

9. “በዚያ ጊዜ ሰዎች ሁሉ የእግዚአብሔርን ስም እንዲጠሩ፣ተስማምተው እንዲያገለግሉት፣አንደበታቸውን አጠራለሁ።

10. ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ፣የሚያመልኩኝ፣ የተበተኑት ሕዝቤቊርባን ያመጡልኛል።

11. በእኔ ላይ ከፈጸማችሁት በደል ሁሉ የተነሣ፣በዚያ ቀን አታፍሩም፤በትዕቢታቸው የሚደሰቱትን፣ከዚህች ከተማ አስወግዳለሁና፤ከእንግዲህ ወዲያ፣በቅዱስ ተራራዬ ላይ አትታበዩብኝም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሶፎንያስ 3