ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሶፎንያስ 2:4-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ጋዛ ባድማ ትሆናለች፤አስቀሎናም ፈራርሳ ትቀራለች፤አዛጦን በቀትር ባዶ ትሆናለች፤አቃሮንም ትነቀላለች።

5. እናንት በባሕር ዳርቻ የምትኖሩ፣የከሊታውያን ሰዎች ሆይ፤ ወዮላችሁየፍልስጥኤማውያን ምድር ከነዓን ሆይ፤በአንቺ ላይ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤“ፍጹም አጠፋሻለሁ፤ከነዋሪዎችሽም የሚተርፍ የለም።”

6. የቀርጤስ ሰዎች የሚኖሩበት በባሕሩዳር ያለው ምድር፣የእረኞች መኖሪያና የበጎች በረት ይሆናል፤

7. ይህም ለይሁዳ ቤት ትሩፍ ይሰጣል፤እነርሱም በዚያ መሰማሪያ ያገኛሉ።በአስቀሎና ቤቶች ውስጥም፣በምሽት ይተኛሉ፤አምላካቸው እግዚአብሔር ይጠብቃቸዋል፤ምርኮአቸውንም ይመልስላቸዋል።

8. “የሞዓብን ስድብ፣የአሞናውያንንም ፌዝ ሰምቻለሁ፤ሕዝቤን ሰድበዋል፤በምድራቸውም ላይ ዝተዋል።

9. ስለዚህ የእስራኤል አምላክ፣ ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“በሕያውነቴ እምላለሁሞዓብ እንደ ሰዶም፣አሞናውያን እንደ ገሞራ፣ዐረም እንደ ዋጠው ቦታና እንደ ጨውጒድጓድ ለዘላለም ጠፍ ይሆናሉ።ከሕዝቤ የቀሩት ይዘርፏቸዋል፤ከወገኔ የተረፉትም ምድራቸውንይወርሳሉ።”

10. ከትዕቢታቸው የተነሣ የሚደርስባቸው ይህ ነው፤የሁሉን ገዥ የእግዚአብሔርን ሕዝብሰድበው ዘብተውበታልና፣

11. እግዚአብሔር የምድሪቱን አማልክትሁሉ በሚደመስስበት ጊዜ፣በእነርሱ ዘንድ የተፈራ ይሆናል፤በየባሕሩ ጠረፍ የሚኖሩ ሕዝቦች፣እያንዳንዳቸው በያሉበት ሆነው ለእርሱ ይሰግዳሉ።

12. “ኢትዮጵያውያን ሆይ፤ እናንተም፣በሰይፌ ትገደላላችሁ።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሶፎንያስ 2