ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሶፎንያስ 2:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እናንት ዕረፍት የሌላችሁ ሕዝብ ሆይ፤በአንድነት ተሰብሰቡ፤ ተከማቹም፤

2. የተወሰነው ጊዜ ሳይደርስ፣ቀኑ እንደ ገለባ ሳይጠራርጋችሁ፣ የእግዚአብሔር ጽኑ ቊጣ በእናንተ ላይ ሳይመጣ፣ የእግዚአብሔር የመዓት ቀንሳይደርስባችሁ ተሰብሰቡ።

3. እናንት የምድር ትሑታን ሁሉ፣ትእዛዙን የምትፈጽሙ፣ እግዚአብሔርን እሹ፤ጽድቅንና ትሕትናን ፈልጉ፤ በእግዚአብሔር የቊጣ ቀን፣ትሰወሩ ይሆናል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሶፎንያስ 2