ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሰቆቃወ 5:7-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. አባቶቻችን ኀጢአት ሠርተው አለፉ፤እኛም የእነርሱን ቅጣት ተሸከምን።

8. ባሮች ሠልጥነውብናል፤ከእጃቸው ነጻ የሚያወጣን ማንም የለም።

9. በምድረ በዳ ካለው ሰይፍ የተነሣ፣በሕይወታችን ተወራርደን እንጀራ አገኘን።

10. ቈዳችን እንደ ምድጃ ጠቍሮአል፤በራብም ተቃጥሎአል።

11. ሴቶች በጽዮን፣ደናግል በይሁዳ ከተሞች ተደፈሩ።

12. መሳፍንት በእነርሱ እጅ ተሰቀሉ፤ሽማግሌዎችም አልተከበሩም።

13. ጐልማሶች ወፍጮ እንዲፈጩ ተገደዱ፤ወንዶች ልጆች በዕንጨት ሸክም ተንገዳገዱ።

14. ሽማግሌዎች ከከተማዪቱ በር ሄደዋል፤ጐልማሶች ዝማሬያቸውን አቁመዋል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሰቆቃወ 5