ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሰቆቃወ 5:14-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. ሽማግሌዎች ከከተማዪቱ በር ሄደዋል፤ጐልማሶች ዝማሬያቸውን አቁመዋል።

15. ደስታ ከልባችን ጠፍቶአል፤ጭፈራችን ወደ ልቅሶ ተለውጦአል።

16. አክሊላችን ከራሳችን ላይ ወድቆአል፤ወዮልን፤ ኀጢአት ሠርተናልና!

17. ከዚህ የተነሣ ልባችን ደከመ፤ከእነዚህ የተነሣም ዐይናችን ፈዘዘ፤

18. ባዶዋን የቀረችው የጽዮን ተራራ፣የቀበሮዎች መፈንጫ ሆናለችና።

19. አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ለዘላለም ትገዛለህ፤ዙፋንህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሰቆቃወ 5