ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሰቆቃወ 5:10-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. ቈዳችን እንደ ምድጃ ጠቍሮአል፤በራብም ተቃጥሎአል።

11. ሴቶች በጽዮን፣ደናግል በይሁዳ ከተሞች ተደፈሩ።

12. መሳፍንት በእነርሱ እጅ ተሰቀሉ፤ሽማግሌዎችም አልተከበሩም።

13. ጐልማሶች ወፍጮ እንዲፈጩ ተገደዱ፤ወንዶች ልጆች በዕንጨት ሸክም ተንገዳገዱ።

14. ሽማግሌዎች ከከተማዪቱ በር ሄደዋል፤ጐልማሶች ዝማሬያቸውን አቁመዋል።

15. ደስታ ከልባችን ጠፍቶአል፤ጭፈራችን ወደ ልቅሶ ተለውጦአል።

16. አክሊላችን ከራሳችን ላይ ወድቆአል፤ወዮልን፤ ኀጢአት ሠርተናልና!

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሰቆቃወ 5