ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሰቆቃወ 5:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ በእኛ ላይ የደረሰውን አስብ፤ውርደታችንን እይ፤ ተመልከትም።

2. ርስታችን ለመጻተኞች፣ቤቶቻችን ለባዕዳን ዐልፈው ተሰጡ።

3. ወላጅ አልባና አባት የሌላቸው ሆንን፤እናቶቻችን እንደ መበለቶች ሆኑ።

4. ለምንጠጣው ውሃ መክፈል ነበረብን፤ዕንጨታችንንም የምናገኘው በግዢ ነበር።

5. የሚያሳድዱን ከተረከዞቻችን ሥር ናቸው፤ተጨንቀናል ዕረፍትም አጥተናል።

6. እንጀራ እንጠግብ ዘንድ፣ለአሦርና ለግብፅ እጃችንን ሰጠን።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሰቆቃወ 5