ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሰቆቃወ 5:1-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ በእኛ ላይ የደረሰውን አስብ፤ውርደታችንን እይ፤ ተመልከትም።

2. ርስታችን ለመጻተኞች፣ቤቶቻችን ለባዕዳን ዐልፈው ተሰጡ።

3. ወላጅ አልባና አባት የሌላቸው ሆንን፤እናቶቻችን እንደ መበለቶች ሆኑ።

4. ለምንጠጣው ውሃ መክፈል ነበረብን፤ዕንጨታችንንም የምናገኘው በግዢ ነበር።

5. የሚያሳድዱን ከተረከዞቻችን ሥር ናቸው፤ተጨንቀናል ዕረፍትም አጥተናል።

6. እንጀራ እንጠግብ ዘንድ፣ለአሦርና ለግብፅ እጃችንን ሰጠን።

7. አባቶቻችን ኀጢአት ሠርተው አለፉ፤እኛም የእነርሱን ቅጣት ተሸከምን።

8. ባሮች ሠልጥነውብናል፤ከእጃቸው ነጻ የሚያወጣን ማንም የለም።

9. በምድረ በዳ ካለው ሰይፍ የተነሣ፣በሕይወታችን ተወራርደን እንጀራ አገኘን።

10. ቈዳችን እንደ ምድጃ ጠቍሮአል፤በራብም ተቃጥሎአል።

11. ሴቶች በጽዮን፣ደናግል በይሁዳ ከተሞች ተደፈሩ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሰቆቃወ 5