ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሰቆቃወ 3:58-65 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

58. ጌታ ሆይ፤ ለእኔ ተሟገትኽልኝ፤ሕይወቴንም ተቤዠህ።

59. እግዚአብሔር ሆይ፤ በእኔ ላይ የተደረገውን ግፍ አየህ፤ፍርዴን ፍረድልኝ!

60. በቀላቸውን ሁሉ፣በእኔም ላይ ያሰቡትን ዐድማ አየህ።

61. እግዚአብሔር ሆይ፤ ስድባቸውን ሁሉ፣በእኔ ላይ ያሰቡትን ዐድማ ሁሉ ሰማህ፤

62. ይህም ቀኑን ሙሉ በእኔ ላይ፣ጠላቶቼ የሚያውጠነጥኑትና የሚያንሾካሹኩት ነው።

63. ተመልከታቸው! ቆመውም ሆነ ተቀምጠው፣በዘፈናቸው ይሣለቁብኛል።

64. እግዚአብሔር ሆይ፤ እጆቻቸው ላደረጉት፣የሚገባውን መልሰህ ክፈላቸው።

65. በልባቸው ላይ መጋረጃን ዘርጋ፤ርግማንህም በላያቸው ይሁን!

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሰቆቃወ 3