ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሰቆቃወ 3:52-58 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

52. ያለ ምክንያት ጠላቶቼ የሆኑ፣እንደ ወፍ አደኑኝ።

53. ሕይወቴን በጒድጓድ ውስጥ ሊያጠፉ ሞከሩ፣ድንጋይም በላዬ አደረጉ።

54. ውሃ ሞልቶ በዐናቴ ላይ ፈሰሰ፤ጠፍቻለሁ ብዬ አሰብሁ።

55. በጥልቁ ጒድጓድ ውስጥ ሳለሁ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ የአንተን ስም ጠራሁ።

56. ልመናዬን ሰምተሃል፤ “ርዳታም ፈልጌ ስጮኽ፣ከመስማት ጆሮህን አትከልክል።”

57. በጠራሁህ ጊዜ ቀረብኸኝ፣እንዲሁም፣ “አትፍራ” አልኸኝ።

58. ጌታ ሆይ፤ ለእኔ ተሟገትኽልኝ፤ሕይወቴንም ተቤዠህ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሰቆቃወ 3