ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሰቆቃወ 3:21-31 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

21. ሆኖም ይህን አስባለሁእንግዲያስ ተስፋ አለኝ፤

22. ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ታላቅ ፍቅር የተነሣ ነው፤ርኅራኄው አያልቅምና።

23. ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ታማኝነትህም ብዙ ነው።

24. ራሴን እንዲህ አልሁት፤ “እግዚአብሔር ዕድል ፈንታዬ ነው፤ስለዚህ ተስፋ አደርገዋለሁ።

25. እርሱን ተስፋ ለሚያደርጉት፣ለሚፈልገውም ሰው እግዚአብሔር መልካም ነው።

26. ሰው የእግዚአብሔርን ማዳን፣ዝም ብሎ ተስፋ ቢያደርግ መልካም ነው።

27. ሰው በወጣትነቱ፣ቀንበር ቢሸከም መልካም ነው።

28. ብቻውን ዝም ብሎ ይቀመጥ፤ እግዚአብሔር አሸክሞታልና።

29. ፊቱን በዐቧራ ውስጥ ይቅበር፤ተስፋ ሊኖር ይችላልና።

30. ጒንጩን ለሚመታው ሰው ይስጥ፤ውርደትንም ይጥገብ።

31. እግዚአብሔር ሰውን፣ለዘላለም አይጥልምና፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሰቆቃወ 3