ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሩት 4:15-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. ልጁ ሕይወትሽን ያድሳታል፤ በእርጅና ዘመንሽም ይጦርሻል፤ የምትወድሽና ከሰባት ወንዶች ልጆች የምትበልጥብሽ ምራትሽ ወልዳዋለችና።”

16. ከዚያም ኑኃሚን ሕፃኑን ተቀብላ ታቀፈችው፤ ሞግዚትም ሆነችው።

17. ጎረቤቶቿ የሆኑ ሴቶችም፣ “ለኑኃሚን ወንድ ልጅ ተወለደላት” አሉ። ስሙንም ኢዮቤድ ብለው ጠሩት፤ እርሱም የዳዊት አባት የሆነው የእሴይ አባት ነበር።

18. እንግዲህ የፋሬስ ቤተ ሰብ ትውልድ ይህ ነው፦ፋሬስ ኤስሮምን ወለደ፤

19. ኤስሮምም አራምን ወለደ፤አራምም አሚናዳብን ወለደ፤

20. አሚናዳብም ነኦሶንን ወለደ፤ነአሶን ሰልሞንን ወለደ፤

21. ሰልሞንም ቦዔዝን ወለደ፤ቦዔዝም ኢዮቤድን ወለደ፤

22. ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፤እሴይም ዳዊትን ወለደ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሩት 4