ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሩት 2:3-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ስለዚህ እርሷም ወጣች፤ ከአጫጆች ኋላ ኋላ እየተከታተለችም ከአዝመራው ቦታ ትቃርም ጀመር፤ እንዳጋጣሚ ትቃርምበት የነበረው አዝመራ ከአቤሜሌክ ጐሣ የሆነው የቦዔዝ ነበር።

4. በዚሁ ጊዜ ቦዔዝ ከቤተ ልሔም መጣ፤ አጫጆቹንም፣ “እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን” ብሎ ሰላምታ ሰጣቸው።እነርሱም፣ “እግዚአብሔር ይባርክህ” ብለው መለሱለት።

5. ከዚያም ቦዔዝ የአጫጆቹን አለቃ፣ “ይህች ወጣት ሴት የማን ናት?” ሲል ጠየቀው።

6. የአጫጆቹም አለቃ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ከኑኃሚን ጋር ከሞዓብ ምድር ተመልሳ የመጣች ሞዓባዊት ናት።

7. እርሷም፣ ‘አጫጆቹን እየተከተልሁ በነዶው መካከል እንድቃርም እባክህ ፍቀድልኝ’ አለችኝ። ለጥቂት ጊዜ በመጠለያው ከማረፏ በስተቀር፣ ወደ አዝመራው ቦታ ገብታ ከጥዋት አንሥቶ እስካሁን ያለ ማቋረጥ ስትቃርም ቈይታለች።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሩት 2