ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 7:23-27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. ፍላጻ ጒበቱን እስኪወጋው ድረስ፣ሕይወቱን እንደሚያሳጣው ሳያውቅ፣በራ ወደ ወጥመድ እንደምትገባ ወፍ ሆነ።

24. ልጆቼ ሆይ፤ አሁንም አድምጡኝ፤የምለውንም ልብ ብላችሁ ስሙኝ።

25. ልባችሁን ወደ መንገዷ አታዘንብሉ፤ወደ ስሕተት ጐዳናዋም አትግቡ።

26. አዋርዳ የጣለቻቸው ብዙ ናቸው፤የገደለቻቸውም ስፍር ቊጥር የላቸውም።

27. ቤቷ ወደ ሲኦል የሚወስድ፣ወደ ሞት ማደሪያም የሚያወርድ ጐዳና ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 7