ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 7:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ልጄ ሆይ፤ ቃሌን ጠብቅ፤ትእዛዜንም በውስጥህ አኑር።

2. ትእዛዜን ጠብቅ፤ በሕይወት ትኖራለህ፤ትምህርቴንም እንደ ዐይንህ ብሌን ተንከባከበው።

3. በጣትህ ላይ እሰረው፤በልብህ ጽላት ላይ ጻፈው።

4. ጥበብን፣ “እኅቴ ነሽ” በላት፤ማስተዋልንም፣ “ዘመዴ ነህ” በለው፤

5. ከአመንዝራ ሴት፣በአንደበቷም ከምታታልል ዘልዛላ ሴት ይጠብቁሃል።

6. በቤቴ መስኮት፣በዐይነ ርግቡ ወደ ውጭ ተመለከትሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 7