ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 7:1-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ልጄ ሆይ፤ ቃሌን ጠብቅ፤ትእዛዜንም በውስጥህ አኑር።

2. ትእዛዜን ጠብቅ፤ በሕይወት ትኖራለህ፤ትምህርቴንም እንደ ዐይንህ ብሌን ተንከባከበው።

3. በጣትህ ላይ እሰረው፤በልብህ ጽላት ላይ ጻፈው።

4. ጥበብን፣ “እኅቴ ነሽ” በላት፤ማስተዋልንም፣ “ዘመዴ ነህ” በለው፤

5. ከአመንዝራ ሴት፣በአንደበቷም ከምታታልል ዘልዛላ ሴት ይጠብቁሃል።

6. በቤቴ መስኮት፣በዐይነ ርግቡ ወደ ውጭ ተመለከትሁ።

7. ማስተዋል የጐደለውን ወጣት፣ብስለት ከሌላቸው መካከል አየሁት፤ከጎልማሶችም መካከል ለየሁት።

8. የቤቷን አቅጣጫ ይዞ፣በቤቷ ማእዘን አጠገብ ባለው መንገድ ያልፍ ነበር፤

9. ቀኑ መሸትሸት ሲል፣በውድቅት ሌሊት፣ በጽኑ ጨለማ።

10. ከዚያም አንዲት ሴት ልታገኘው ወጣች፤እንደ ዝሙት አዳሪ ለብሳ፣ ለማሳሳት ታጥቃ።

11. ጯኺና ማን አለብኝ ባይ ናት፤እግሮቿ አርፈው ቤት አይቀመጡም፤

12. አንዴ በመንገድ፣ አንዴ በአደባባይ፤በየማእዘኑም ታደባለች።

13. አፈፍ አድርጋ ይዛ ሳመችው፤ኀፍረቷንም ጥላ እንዲህ አለችው፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 7