ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 4:8-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. ክብርን ስጣት፤ ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፤ዕቀፋት፤ ታከብርሃለች፤

9. በራስህ ላይ ሞገሳማ አክሊል ትደፋልሃለች፤የክብር ዘውድም ታበረክትልሃለች።

10. ልጄ ሆይ፤ አድምጠኝ፤ ቃሌንም ልብ በል፤የሕይወት ዘመንህም ትበዛለች።

11. በጥበብ ጐዳና አስተምርሃለሁ፤ቀጥተኛውንም መንገድ አሳይሃለሁ።

12. ስትሄድ ርምጃህ አይሰናከልም፤ስትሮጥም አትደናቀፍም።

13. ምክርን አጥብቀህ ያዛት፤ አትልቀቃት፤ጠብቃት፤ ሕይወትህ ናትና።

14. ወደ ኀጥኣን ጐዳና እግርህን አታንሣ፤በክፉ ሰዎች መንገድ አትሂድ፤

15. ከዚያ አትድረስ፤ አትጓዝበት፤ሽሸው፤ መንገድህን ይዘህ ሂድ፤

16. ክፉ ካላደረጉ አይተኙምና፤ሰውን ካላሰናከሉ እንቅልፍ ባይናቸው አይዞርም።

17. የክፋት እንጀራ ይበላሉ፤የዐመፅ ወይን ጠጅ ይጠጣሉ።

18. የጻድቃን መንገድ ሙሉ ቀን እስኪሆን ድረስ፣ብርሃኑ እየጐላ እንደሚሄድ የማለዳ ውጋጋን ነው።

19. የክፉዎች መንገድ ግን እንደ ድቅድቅ ጨለማ ነው፤ምን እንደሚያሰናክላቸውም አያውቁም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 4