ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 4:20-27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. ልጄ ሆይ፤ የምነግርህን አስተውል፤ቃሌንም በጥንቃቄ አድምጥ።

21. ከእይታህ አታርቀው፤በልብህም ጠብቀው፤

22. ለሚያገኘው ሕይወት፤ለመላው የሰው አካልም ጤንነት ነውና።

23. ከሁሉም በላይ ልብህን ጠብቅ፤የሕይወት ምንጭ ነውና።

24. ጥመትን ከአፍህ አስወግድ፤ብልሹ ንግግርም ከከንፈሮችህ ይራቅ።

25. ዐይኖችህ በቀጥታ ይመልከቱ፤ትክ ብለህም ፊት ለፊት እይ።

26. የእግርህን ጐዳና አስተካክል፤የጸናውን መንገድ ብቻ ያዝ።

27. ወደ ቀኝ ወደ ግራ አትበል፤እግርህን ከክፉ ጠብቅ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 4