ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 4:11-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. በጥበብ ጐዳና አስተምርሃለሁ፤ቀጥተኛውንም መንገድ አሳይሃለሁ።

12. ስትሄድ ርምጃህ አይሰናከልም፤ስትሮጥም አትደናቀፍም።

13. ምክርን አጥብቀህ ያዛት፤ አትልቀቃት፤ጠብቃት፤ ሕይወትህ ናትና።

14. ወደ ኀጥኣን ጐዳና እግርህን አታንሣ፤በክፉ ሰዎች መንገድ አትሂድ፤

15. ከዚያ አትድረስ፤ አትጓዝበት፤ሽሸው፤ መንገድህን ይዘህ ሂድ፤

16. ክፉ ካላደረጉ አይተኙምና፤ሰውን ካላሰናከሉ እንቅልፍ ባይናቸው አይዞርም።

17. የክፋት እንጀራ ይበላሉ፤የዐመፅ ወይን ጠጅ ይጠጣሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 4