ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 4:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ልጆቼ ሆይ፤ የአባትን ምክር አድምጡ፤ልብ ብላችሁ ስሙ፤ ማስተዋልንም ገንዘብ አድርጉ።

2. በጎ ትምህርት እሰጣችኋለሁ፤ስለዚህ ትምህርቴን አትተዉ።

3. በአባቴ ቤት ገና ለግላጋ ወጣት፣ለእናቴም አንድ ልጇ ብቻ በነበርሁ ጊዜ፣

4. አባቴ እንዲህ ሲል አስተማረኝ፤“ቃሌን በሙሉ በልብህ ያዝ፤ትእዛዜንም ጠብቅ፤ በሕይወት ትኖራለህ።

5. ጥበብን አግኛት፤ ማስተዋልን ያዛት፤ቃሌን አትርሳ፤ ከእርሷም ዘወር አትበል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 4