ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 30:24-33 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

24. “በምድር ላይ አራት ነገሮች ትንንሽ ናቸው፤ሆኖም እጅግ ጠቢባን ናቸው፤

25. ጒንዳኖች ደካማ ፍጡራን ናቸው፤ሆኖም ምግባቸውን በበጋ ያከማቻሉ።

26. ሽኮኮዎች ዐቅመ ደካማ ናቸው፤ሆኖም መኖሪያቸውን በቋጥኞች መካከል ይሠራሉ፤

27. አንበጦች ንጉሥ የላቸውም፤ሆኖም ቅደም ተከተል ይዘው ይጓዛሉ፤

28. እንሽላሊት በእጅ ትያዛለች፤ሆኖም በቤተ መንግሥት ትገኛለች።

29. “አረማመዳቸው ግርማዊ የሆነ ሦስት ነገሮች አሉ፤እንዲያውም በሞገስ የሚጐማለሉ አራት ናቸው፤

30. ከአራዊት መካከል ኀይለኛ የሆነው፣ከምንም ነገር ፊት ግንባሩን የማያጥፈው አንበሳ፤

31. ጐርደድ ጐርደድ የሚል አውራ ዶሮ፣ አውራ ፍየል፣እንዲሁም በሰራዊቱ የታጀበ ንጉሥ ናቸው።

32. ተላላ ሆነህ ራስህን ከፍ ከፍ ካደረግህ፣ወይም ክፉ ነገር ካቀድህ፣እጅህን በአፍህ ላይ አድርግ።

33. ወተት ሲናጥ ቅቤ እንደሚወጣው፣አፍንጫን ሲያሹት እንደሚደማ፣ቊጣን ማነሣሣትም ጥልን ይፈጥራል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 30