ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 30:17-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. “በአባት ላይ የምታፌዝ ዐይን፣የእናትንም ትእዛዝ የምትንቅ፣የሸለቆ ቊራዎች ይጐጠጒጧታል፤ጆፌ አሞሮችም ይበሏታል።

18. “እጅግ የሚያስደንቁኝ ሦስት ነገሮች አሉ፤የማላስተውላቸውም አራት ናቸው፤

19. የንስር መንገድ በሰማይ፣የእባብ መንገድ በቋጥኝ፣የመርከብ መንገድ በባሕር፣የሰውም መንገድ ከሴት ልጅ ጋር ናቸው።

20. “የአመንዝራዪቱ መንገድ ይህ ነው፤በልታ አፏን በማበስ፣‘ምንም የሠራሁት ጥፋት የለም’ ትላለች።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 30