ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 30:10-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. “አገልጋይን በጌታው ፊት በክፉ አታንሣው፤አለዚያ ይረግምህና ጒዳት ያገኝሃል።

11. “አባቱን የሚረግም፣እናቱን የማይባርክ ትውልድ አለ፤

12. ራሳቸውን ንጹሓን አድርገው የሚቈጥሩ፣ሆኖም ከርኵሰታቸው ያልነጹ አሉ፤

13. ዐይናቸው ትዕቢተኛ የሆነ፣ አስተያያቸው ንቀት የሞላበት፣

14. ድኾችን ከምድር፣ችግረኞችንም ከሰው ዘር መካከል ለማጥፋት፣ጥርሳቸው ሰይፍ የሆነ፣መንጋጋቸውም ካራ የሆነ አሉ።

15. “አልቅት ሁለት ሴት ልጆች አሉት፤‘ስጡን! ስጡን!’ እያሉ ይጮኻሉ፤“ፈጽሞ የማይጠግቡ ሦስት ነገሮች አሉ፤‘በቃኝን’ ከቶ የማያውቁ አራት ናቸው፤

16. እነርሱም መቃብር፣ መካን ማሕፀን፣ውሃ ጠጥታ የማትረካ ምድር፣‘በቃኝ’ የማይል እሳት ናቸው።

17. “በአባት ላይ የምታፌዝ ዐይን፣የእናትንም ትእዛዝ የምትንቅ፣የሸለቆ ቊራዎች ይጐጠጒጧታል፤ጆፌ አሞሮችም ይበሏታል።

18. “እጅግ የሚያስደንቁኝ ሦስት ነገሮች አሉ፤የማላስተውላቸውም አራት ናቸው፤

19. የንስር መንገድ በሰማይ፣የእባብ መንገድ በቋጥኝ፣የመርከብ መንገድ በባሕር፣የሰውም መንገድ ከሴት ልጅ ጋር ናቸው።

20. “የአመንዝራዪቱ መንገድ ይህ ነው፤በልታ አፏን በማበስ፣‘ምንም የሠራሁት ጥፋት የለም’ ትላለች።

21. “ምድር በሦስት ነገር ትናወጣለች፤እንዲያውም መሸከም የማትችላቸው አራት ነገሮች ናቸው፤

22. ባሪያ ሲነግሥ፣ሰነፍ እንጀራ ሲጠግብ፣

23. የተጠላች ሴት ባል ስታገባ፣ሴት ባሪያ በእመቤቷ እግር ስትተካ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 30