ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 29:20-27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. በችኰላ የሚናገርን ሰው ታያለህን?ከእርሱ ይልቅ ተላላ ተስፋ አለው።

21. ሰው አገልጋዩን ከልጅነቱ ጀምሮ ቢያቀማጥል፣የኋላ ኋላ ሐዘን ያገኘዋል።

22. ቊጡ ሰው ጠብን ይጭራል፤ግልፍተኛም ብዙ ኀጢአት ይሠራል።

23. ሰውን ትዕቢቱ ያዋርደዋል፤ ትሑት መንፈስ ያለው ግን ክብርንይጐናጸፋል።

24. የሌባ ግብረ አበር የገዛ ራሱ ጠላት ነው፤የመሐላውን ርግማን እየሰማ ጭጭ ይላል።

25. ሰውን መፍራት ወጥመድ ነው፤ በእግዚአብሔር የሚታመን ግን በሰላም ይኖራል።

26. ብዙዎች በገዥ ፊት ተደማጭነት ማግኘት ይሻሉ፤ሰው ፍትሕ የሚያገኘው ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።

27. ጻድቃን አታላዮችን ይጸየፋሉ፤ክፉዎችም ቅኖችን ይጠላሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 29