ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 29:15-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. የተግሣጽ በትር ጥበብን ታጐናጽፋለች፤መረን የተለቀቀ ልጅ ግን እናቱን ያሳፍራል።

16. ክፉዎች ሥልጣን ሲይዙ ኀጢአት ይበዛል፤ጻድቃን ግን የእነርሱን ውድቀት ያያሉ።

17. ልጅህን ቅጣው፤ ሰላም ይሰጥሃል፤ነፍስህንም ደስ ያሰኛታል።

18. ራእይ በሌለበት ሕዝብ መረን ይሆናል፤ሕግን የሚጠብቅ ግን የተባረከ ነው።

19. አገልጋይ በቃል ብቻ ሊታረም አይችልም፤ቢያስተውለውም እንኳ በጀ አይልም።

20. በችኰላ የሚናገርን ሰው ታያለህን?ከእርሱ ይልቅ ተላላ ተስፋ አለው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 29