ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 29:11-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ተላላ ሰው ቊጣውን ያለ ገደብ ይለቀዋል፤ጠቢብ ሰው ግን ራሱን ይቈጣጠራል።

12. ገዥ የሐሰት ወሬ የሚሰማ ከሆነ፣ሹማምቱ ሁሉ ክፉዎች ይሆናሉ።

13. ድኻውና ጨቋኙ የጋራ ነገር አላቸው፤ እግዚአብሔር ለሁለቱም የዐይን ብርሃንን ሰጥቶአቸዋል።

14. ንጉሥ ለድኻ ትክክለኛ ፍርድ ቢሰጥ፣ዙፋኑ ዘላለም ጸንቶ ይኖራል።

15. የተግሣጽ በትር ጥበብን ታጐናጽፋለች፤መረን የተለቀቀ ልጅ ግን እናቱን ያሳፍራል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 29