ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 29:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ከብዙ ተግሣጽ በኋላ ዐንገቱን የሚያደነድን ሰው፣በድንገት ይጠፋል፤ መዳኛም የለውም።

2. ጻድቃን ሥልጣን ሲይዙ ሕዝብ ሐሤት ያደርጋል፤ክፉዎች ሲገዙ ግን ሕዝብ ያቃስታል።

3. ጥበብን የሚወድ ሰው አባቱን ደስ ያሰኛል፤የአመንዝራዎች ወዳጅ ግን ሀብቱን ያባክናል።

4. ፍትሕን በማስፈን ንጉሥ አገርን ያረጋጋል፤ጒቦ ለማግኘት የሚጐመጅ ግን ያፈራርሳታል።

5. ባልንጀራውን የሚሸነግል፣ለገዛ እግሩ መረብ ይዘረጋል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 29