ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 28:6-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. በአካሄዱ ነውር የሌለበት ድኻ፣መንገዱ ጠማማ ከሆነ ባለጠጋ ይሻላል።

7. ሕግን የሚጠብቅ አስተዋይ ልጅ ነው፤ከሆዳሞች ጋር ጓደኛ የሚሆን ግን አባቱን ያዋርዳል።

8. በከፍተኛ ወለድ ሀብቱን የሚያካብት፣ለድኻ ለሚራራ፣ ለሌላው ሰው ያከማችለታል።

9. ሕግን ላለመስማት ጆሮውን የሚደፍን፣ጸሎቱ እንኳ አስጸያፊ ነው።

10. ቅኖችን በክፉ መንገድ የሚመራ፣በቈፈረው ጒድጓድ ይገባል፤ንጹሓን ግን መልካም ነገርን ይወርሳሉ።

11. ባለጠጋ ራሱን ጠቢብ አድርጎ ይቈጥር ይሆናል፤አስተዋይ የሆነ ድኻ ግን መርምሮ ያውቀዋል።

12. ጻድቃን ድል ሲነሡ ታላቅ ደስታ ይሆናል፤ክፉዎች ሥልጣን ሲይዙ ግን ሕዝብ ይሸሸጋል።

13. ኀጢአቱን የሚሰውር አይለማም፤የሚናዘዝና የሚተወው ግን ምሕረትን ያገኛል።

14. እግዚአብሔርን ዘወትር የሚፈራ ሰው ቡሩክ ነው፤ልቡን የሚያደነድን ግን መከራ ላይ ይወድቃል።

15. ታዳጊ በሌለው ሕዝብ ላይ የተሾመ ጨካኝ ገዥ፣እንደሚያገሣ አንበሳ ወይም ተንደንድሮ እንደሚይዝ ድብ ነው።

16. ጨካኝ ገዥ ማመዛዘን ይጐድለዋል፤ያላግባብ የሚገኝን ጥቅም የሚጸየፍ ግን ዕድሜው ይረዝማል።

17. የሰው ደም ያለበት ሰው፣ዕድሜ ልኩን ሲቅበዘበዝ ይኖራል፤ማንም ሰው አይርዳው።

18. አካሄዱ ነቀፋ የሌለበት ሰው ክፉ አያገኘውም፤መንገዱ ጠማማ የሆነ ግን ድንገት ይወድቃል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 28