ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 28:18-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

18. አካሄዱ ነቀፋ የሌለበት ሰው ክፉ አያገኘውም፤መንገዱ ጠማማ የሆነ ግን ድንገት ይወድቃል።

19. መሬቱን የሚያርስ የተትረፈረፈ ምግብ ያገኛል፤ከንቱ ተስፋን ይዞ የሚጓዝ ግን ድኽነትን ይወርሳል።

20. ታማኝ ሰው እጅግ ይባረካል፤ሀብት ለማግኘት የሚጣደፍ ግን ከቅጣት አያመልጥም።

21. አድልዎ ማድረግ መልካም አይደለም፤ሰው ግን ለቊራሽ እንጀራ ሲል በደል ይፈጽማል።

22. ስስታም ሀብት ለማከማቸት ይስገበገባል፤ድኽነት እንደሚጠብቀውም አያውቅም።

23. ሸንጋይ አንደበት ካለው ይልቅ፣ሰውን የሚገሥጽ ውሎ ዐድሮ ይወደዳል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 28