ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 28:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ክፉ ሰው ማንም ሳያሳድደው ይሸሻል፤ጻድቅ ግን እንደ አንበሳ ልበ ሙሉ ነው።

2. አገር ስታምፅ፣ ገዦቿ ይበዛሉ፤አስተዋይና ዐዋቂ ሰው ግን ሥርዐትን ያሰፍናል።

3. ድኾችን የሚያስጨንቅ ሰው፣ሰብል እንደሚያጠፋ ኀይለኛ ዝናብ ነው።

4. ሕግን የሚተዉ ክፉዎችን ያወድሳሉ፤ሕግን የሚጠብቁ ግን ይቋቋሟቸዋል።

5. ክፉዎች ፍትሕን አያስተውሉም፤ እግዚአብሔርን የሚሹ ግን ሙሉ በሙሉ ያውቁታል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 28