ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 28:1-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ክፉ ሰው ማንም ሳያሳድደው ይሸሻል፤ጻድቅ ግን እንደ አንበሳ ልበ ሙሉ ነው።

2. አገር ስታምፅ፣ ገዦቿ ይበዛሉ፤አስተዋይና ዐዋቂ ሰው ግን ሥርዐትን ያሰፍናል።

3. ድኾችን የሚያስጨንቅ ሰው፣ሰብል እንደሚያጠፋ ኀይለኛ ዝናብ ነው።

4. ሕግን የሚተዉ ክፉዎችን ያወድሳሉ፤ሕግን የሚጠብቁ ግን ይቋቋሟቸዋል።

5. ክፉዎች ፍትሕን አያስተውሉም፤ እግዚአብሔርን የሚሹ ግን ሙሉ በሙሉ ያውቁታል።

6. በአካሄዱ ነውር የሌለበት ድኻ፣መንገዱ ጠማማ ከሆነ ባለጠጋ ይሻላል።

7. ሕግን የሚጠብቅ አስተዋይ ልጅ ነው፤ከሆዳሞች ጋር ጓደኛ የሚሆን ግን አባቱን ያዋርዳል።

8. በከፍተኛ ወለድ ሀብቱን የሚያካብት፣ለድኻ ለሚራራ፣ ለሌላው ሰው ያከማችለታል።

9. ሕግን ላለመስማት ጆሮውን የሚደፍን፣ጸሎቱ እንኳ አስጸያፊ ነው።

10. ቅኖችን በክፉ መንገድ የሚመራ፣በቈፈረው ጒድጓድ ይገባል፤ንጹሓን ግን መልካም ነገርን ይወርሳሉ።

11. ባለጠጋ ራሱን ጠቢብ አድርጎ ይቈጥር ይሆናል፤አስተዋይ የሆነ ድኻ ግን መርምሮ ያውቀዋል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 28