ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 16:10-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. የንጉሥ ከንፈሮች እንደ አምላክ ቃል ይናገራሉ፤አንደበቱ ፍትሕን ያዛባ ዘንድ አይገባም።

11. ሐቀኛ መስፈሪያና ሚዛን ከእግዚአብሔር ናቸው፤በከረጢት ውስጥ ያሉት መመዘኛዎችም ሁሉ ሥራዎቹ ናቸው።

12. ክፋትን ማድረግ ለነገሥታት አጸያፊ ነው፤ዙፋን የሚጸናው በጽድቅ ነውና።

13. ነገሥታት በታማኝ ከንፈሮች ደስ ይላቸዋል፤እውነት የሚናገረውን ሰው ይወዱታል።

14. የንጉሥ ቊጣ የሞት መልእክተኛ ነው፤ጠቢብ ሰው ግን ቊጣውን ያበርዳል።

15. የንጉሥ ፊት ሲፈካ ሕይወት አለ፤በጎነቱም ዝናብ እንዳዘለ የበልግ ደመና ነው።

16. ከወርቅ ይልቅ ጥበብን ማግኘት፣ከብርም ማስተዋልን መምረጥ ምንኛ ይበልጣል!

17. የቅኖች ጐዳና ከክፋት የራቀ ነው፤መንገዱንም የሚጠብቅ ሕይወቱን ይጠብቃል።

18. ትዕቢት ጥፋትን፣የእብሪት መንፈስም ውድቀትን ትቀድማለች።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 16