ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 14:19-31 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. ክፉዎች በደጎች ፊት፣ኀጥኣንም በጻድቃን ደጅ ያጐነብሳሉ።

20. ድኾችን ወዳጆቻቸው እንኳ ይጠሏቸዋል፤ባለጠጎች ግን ብዙ ወዳጆች አሏቸው።

21. ጎረቤቱን የሚንቅ ኀጢአት ይሠራል፤ለተቸገሩት የሚራራ ግን ቡሩክ ነው።

22. ክፉ ነገር የሚያቅዱ ከትክክለኛው መንገድ ይወጡ የለምን?በጎ ነገር የሚያቅዱ ግን ፍቅርንና ታማኝነትን ያተርፋሉ።

23. ለፍተው የሠሩት ሁሉ ትርፍ ያስገኛል፤ከንቱ ወሬ ግን ወደ ድኽነት ያመራል።

24. ጠቢባን ብልጥግና ዘውዳቸው ነው፤የተላሎች ተላላነት ግን ፍሬው ከንቱነት ነው።

25. እውነተኛ ምስክር ሕይወት ያድናል፤ሐሰተኛ ምስክር ግን አባይ ነው።

26. እግዚአብሔርን የሚፈራ ጽኑ አምባ አለው፤ልጆቹም መጠጊያ ይኖራቸዋል።

27. እግዚአብሔርን መፍራት የሕይወት ምንጭ ነው፤ሰውን ከሞት ወጥመድ ያድነዋል።

28. የሕዝብ ብዛት የንጉሥ ክብር ሲሆን፣የዜጐች ማነስ ግን ለገዥ መጥፊያው ነው።

29. ታጋሽ ሰው ትልቅ ማስተዋል አለው፤ግልፍተኛ ሰው ግን ቂልነትን ይገልጣል።

30. ሰላም ያለው ልብ ለሰውነት ሕይወት ይሰጣል፤ቅናት ግን ዐጥንትን ያነቅዛል።

31. ድኾችን የሚያስጨንቅ ፈጣሪያቸውን ይንቃል፤ለተቸገሩ የሚራራ ሁሉ ግን አምላክን ያከብራል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 14