ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 14:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ጠቢብ ሴት ቤቷን ትሠራለች፤ተላላ ሴት ግን በገዛ እጇ ታፈርሰዋለች።

2. አካሄዱ ቅን የሆነ ሰው እግዚአብሔርን ይፈራል፤መንገዱ ጠማማ የሆነ ግን ይንቀዋል።

3. የተላላ ሰው ንግግር ለጀርባው በትር ታስከትልበታለች፤የጥበበኛ ከንፈር ግን ትጠብቃቸዋለች።

4. በሬዎች በሌሉበት ገንዳው ባዶ ይሆናል፤በበሬ ጒልበት ግን ብዙ ምርት ይገኛል።

5. ታማኝ ምስክር አይዋሽም፤ሐሰተኛ ምስክር ግን ውሸትን ይዘከዝካል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 14