ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 13:9-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. የጻድቃን ብርሃን ደምቆ ይበራል፤የክፉዎች መብራት ግን ይጠፋል።

10. ትዕቢት ጠብን ብቻ ያስፋፋል፤ጥበብ ግን ምክርን በሚቀበሉ ዘንድ ትገኛለች።

11. ያላግባብ የተገኘ ገንዘብ እየተመናመነ ያልቃል፤ገንዘቡን ጥቂት በጥቂት የሚያከማች ግን ይጠራቀምለታል።

12. ለነገ የሚባል ተስፋ ልብን ያሳምማል፤የተሳካ ምኞት ግን የሕይወት ዛፍ ነው።

13. ምክርን የሚያቃልል በራሱ ላይ ጥፋት ያመጣል፤ትእዛዝን የሚያከብር ግን ወሮታን ይቀበላል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 13